ኤጀንሲው በ2017ዓ.ም የከተማው የላቀ ቀዳሚ ተ...

image description
image description
- In Service    0

ኤጀንሲው በ2017ዓ.ም የከተማው የላቀ ቀዳሚ ተቋም ለመሆን አቅዶ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ

ኤጀንሲው በ2017ዓ.ም የከተማው የላቀ ቀዳሚ ተቋም ለመሆን አቅዶ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ

CRRSA: ነሃሴ 6/2016ዓ.ም 
አዲስ አበባ

የኤጀንሲው ጠቅላላ ካውንስል ተቋሙ ባስመዘገበው የላቀ አፈፃፀም ውጤት እውቅና እና የቀጣይ የሪፎርም አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አደረገ። 

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ካውንስሉ ለውጤቱ መገኘት ላደረገው ከፍተኛ ጥረት ያመሰገኑ ሲሆን ውጤቱ ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ ያለው ሙያተኛ የጋራ ትጋት ውጤት መሆኑን አንስተዋል። 

ውይይቱ በ2017ዓ.ም ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን ቅሬታ ሙሉ ለሙሉ የሚፈቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በተያዘው የ2017ዓ.ም በጀት ዓመት የከተማው ቀዳሚ እና የላቀ ተቋም ለመሆን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ደርሷል። 

በተገኘው እውቅና ላይ ተነሳሽነትን ለመፍጠር በማዕከል የተደረገው ውይይት እስከ ወረዳ ድረስ እየተደረገ ይገኛል። 

አዲስ የአገልግሎት ምዕራፍ በአዲስ ጅማሮ! 

ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን

ዩትዩብ (youtube)፡

ፌስቡክ/Facebook

ቴሌግራም/ (telegram):

ፖስታ ሳ.ቁ (Box No)፡ 20320


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments